Search

ኢትዮጵያ በሩብ ዓመቱ ከውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከ961 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች

ሰኞ ኅዳር 22, 2018 96

ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 961 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (/) ተናግረዋል።

ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ7 በመቶ በላይ ዕድገት ማሳየቱን ኮሚሽነሩ ለአቢሲ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በሰጡት መረጃ ገልጸዋል።

በልዩኢኮኖሚ ዞኖች ከሚገኙ ኢንቨስትመንቶችም በሩብ ዓመቱ ከወጪ ንግድ 49 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን አክለዋል።

ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ113 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል።

በሩብ ዓመቱ ኮሚሽኑ 123 የውጭ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱንም ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት።

ባለፈው ዓመት ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት በሆነው በገቢና ወጪ ንግድ ላይም ባለፉት 3 ወራት 34 ባለሃብቶች መሳተፋቸውን አንስተዋል።

ባለሃብቶች የሚያነሷቸውን ቅሬታዎች ለመፍታት እና -ተገማች የሆኑ የሕግ እና አሠራር ችግሮችን ለመፍታት  ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት እናክልሎች ጋር  በትብብር በመሠራቱ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በየተመኙሽ አያሌው

#ebcdotstream #Ethiopia #investment #fdi