Search

የእንችላለን ሥነ-ልቦና የተገነባበት የፕሮጀክት አፈፃፀም አቅም

ማክሰኞ ኅዳር 23, 2018 103

የዕቅድን ወደ መሬት ማውረድ እና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን መፈፀም የመደመር መንግሥት መለያው ስለመሆኑ የፕራግማ ካፒታልስ መስራች እና ሥራ አስኪያጅ መርዕድ ፍቅረዮሃንስ ይገልፃሉ፡፡
ከዚህ ቀደም የነበረው ጀምሮ ያለመፈፀም ጎጂ የሥራ ባህል በመቀረፉ፣ ዳጎስ ያለ የውጭ ምንዛሬ በማፍሰስ ከሌሎች ሀገራት የምናስገባቸውን የውጪ ምርቶች ራሳችን ወደ ማምረት እንድንሸጋገር አስችሏል ሲሉ ሥራ አስኪያጁ ከኢቢሲ አዲስ ቀን መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡
በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የፕሬዚዳንት ፅሕፈት ቤት ኃላፊ እና የሕዝብ አስተዳድር መምህር የሆኑት አየለ አዳቶ በበኩላቸው፤ የዜጎችን ተጠቃሚነትን የሚጨምሩ ፕሮጀክቶች የእንችላለን ሥነ-ልቦና የሚገነባባቸው ስለመሆናቸው ያነሳሉ፡፡
የሀገር መቻል እና በራስ አቅም መቆም የዜጎች ሥነ-ልቦ ላይ በጎ አሻራ እንደሚያኖር ገልፀው፤ ይህም ዓለም አቀፋዊ ቅቡልነትን የሚያጎለብት ስለመሆኑ ነው የጠቀሱት፡፡
የሀገር ፕሮጀክት መፈፀም እና የመከወን አቅም ባለፈው ጊዜ የተሰሩ ስህተቶችን ማረም የሚያስችል መሆኑን አመላክተው፤ ዜጎች የተሻለ ነገን እንዲያስቡ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
ኃላፊው አያይዘውም ከዚህ ጎን ለጎን የውስጥ አንድነት እና ሰላም መስፈን ለግዙፍ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ እና ለሀገር እድገት ትልቅ ድርሻ ስላለው ሁሉም ሊጠብቀው ይገባል ብለዋል፡፡
በአፎሚያ ክበበው