Search

በማያቋርጥ የ“መፍጠር እና መፍጠን” መርህ እየሠራን የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እሑድ ኅዳር 28, 2018 47

በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታበሚል መሪ ሀሳብ ለተከታታይ ቀናት በመዲናዋ አዲስ አበባ ሲሰጥ የቆየው 3 ዙር የወረዳ አመራር ስልጠና በውጤታማነት መጠናቀቁን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

ሁነቱ አመራሩ በቀረቡ የስልጠና ሰነዶችና በመስክ ምልከታዎች ተጨማሪ አቅም የገነባበት፣ እርስ በርስ ልምድ በመለዋወጥ የተማማረበት፣ የግንዛቤ አድማሱን ያሰፋበት፣ ለአዲስ ግብ እና ስኬት የተዘጋጀበት፣ መነሳሳትን የፈጠረ የስልጠና መድረክ እንደነበር ገልጸዋል።

መድረኩ በቀጣይም አመራራችን በስልጠናው ያገኘውን ግንዛቤ በተጨባጭ መሬት ማውረድ፣ ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል መቀየር፣ በዚህም ያለምነው ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን እንዲሆን በተሻሻለ የሥራ ባህል 24/7 መትጋት እንደሚገባ መግባባት የፈጠርንበት ነው ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

ለሕዝባችን የምንሰጠውን አገልግሎት ፍትሃዊነት ማረጋገጥ እና ማላቅ፣ በከተማችን ነዋሪዎች ዘንድ ያለውን አዳጊ የልማት ፍላጎት እና ለዘመናት የተከማቸ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመፍታት ራስን ማዘጋጀት፣ እንዲሁም በማያቋርጥ ራስን የማብቃት፣ የፈጠራና የፍጥነት ዑደት ውስጥ ማለፍ እንደሚገባም መግባባት ተፈጥሯል ብለዋል።

በዋናነትም በትኩረት መስክነት በለየናቸው አገራዊ የግብርና እና ገጠር ትራንስፎርሜሽን፣ የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝምና ከተማ ልማት ዘርፎች እመርታ ለማስመዝገብ እንዲቻል ከአመራሩ የሚጠበቁ የመሪነት ሚናዎችን እንዲወጣ ለማድረግ የጋራ መግባባት የፈጠርንበት ስኬታማ የስልጠና መድረክ ነበር ነው ያሉት።

በማያቋርጥ የ“መፍጠር እና መፍጠንመርህ እየሠራን የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት።