በኦሮሚያ ክልል የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ዘመቻ ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በዘንድሮው (2018) በጀት ዓመት በ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ለማከናወን መታቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ገልጸዋል።
በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራውን በስኬት ለማከናወን ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።
የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎቹ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው መሬቶችን ወደ ልማት በማስገበት ረገድ ትልቅ ሚና እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን፤ በዚህም በክልሉ ከ7 ዓመት በፊት 17 በመቶ ብቻ የነበረውን የደን ሽፋን አሁን ላይ 29 በመቶ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል።

ቀደም ባሉት ዓመታትም የተራቆቱ አካባቢዎች ላይ የእርከን ሥራዎችን በማከናወን በጎርፍ ሲሸርሸር የነበረ መሬትን ከአፈር መከላት መከላከል እንደተቻለ አንስተዋል።
በክልሉ የተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የአካባቢን ሥነ-ምህዳር ከመጠበቃቸው ባለፈ የከርሰ ምድርና ገጸ ምድር ውሃ ሀብት እንዲጨምር ማድረጉን አክለዋል።
የዘንድሮው የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ የሚከናወንባቸው ተፋሰሶች የተለዩ ሲሆን፤ ለሥራው ውጤታማነት ይረዳ ዘንድ በክልሉ ለማገኙ የግብርና ባለሞያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠትም ተጀምሯል።
በሂሩት እምቢአለ
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #Oromia #soilandwater #conservation