Search

ከድርቅ ተፈናቃይነት በመስኖ እርሻ ውጤታማ ወደ መሆን የተሸጋገሩት የቦረና አርብቶ አደሮች

ዓርብ ታኅሣሥ 03, 2018 28

በኦሮሚያ ክልል የቦረና ዞን አርብቶ አደሮች የሚታወቁበት መተዳደሪያቸው የእንስሳት እርባታ ሲሆን በዘላቂነት ድርቅ ለመቋቋም የሚያስችሉ የግብርና መሠረተ ልማት እጥረት በመኖሩ ተጎጂዎች ሆነው ቆይተዋል።
በተደጋጋሚ የድርቅ ተጠቂነት ችግር ውስጥ የሚወድቁት አርብቶ አደሮቹ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያቸውን በበጋ መስኖ እርሻ የተደገፈ ለማድረግ እና ኑሯቸውን ለማሻሻል እየተጉ ይገኛሉ።
ለዚህም የመደመር መንግሥት የውኃ አማራጮችን በቦይ ጠልፈው ወደ ማሳቸው በማስገባት ወደ እርሻ ሥራ የሚገቡበትን ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል።
 
አርብቶ አደሮች ሰብሎችን በማምረት ጎተራ ለመሙላት፣ ከብቶችን በባህላዊ መንገድ ከማርባት ወደ ዘመናዊ የማድለብ ሥራ እንዲገቡ እንዲሁም የዶሮ እርባታ በመጀመር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል የተቀናጀ ሥራ የሚሠሩበት አግባብ እንደተፈጠረላቸው ይናገራሉ።
 
መሠረተ ልማቱ ተዘርግቶ ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ ከብቶችን በማድለብ ሥራ የተሰማሩ አርብቶ አደሮቹ ዛሬ ላይ አንድ ሰንጋ በማድለብ እስከ 180 ሺህ ብር ድረስ በመሸጥ ተጠቃሚነታቸውን እያረጋገጡ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ከዚህ ቀደም አርብቶ አደሮቹን የበጋ ስንዴ ወደ ማምረት ሥራ ለማስገባት ልምድ እና ተሞክሮ እንዳልነበራቸው የገለጹት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሰላም፣ ወደዚያው ለመግባት ችግር አጋጥሞአቸው እንደነበር ያስታውሳሉ።
በሂደት በተሠራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራም ከእርባታ ጎን ለጎን እንዴት የበጋ መስኖ እና የዶሮ እርባታ ማከናወን እና ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ተረድተው ወደ ሥራ መግባታቸውን ነው የተናገሩት።
የመደመር መንግሥት የአርብቶ አደሩን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የነደፈው የግብርና ስትራቴጂ ውጤታማ መሆኑን በስፍራው ተገኝተው ምልከታ ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ሳዳት ነሻ በበኩላቸው በተሠራው ሥራ ተጨባጭ ውጤቶች እየተገኙ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በመሐመድ ፊጣሞ
All reactions:
30