Search

የሥነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ ሠራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ማክሰኞ ታኅሣሥ 07, 2018 42

2018 የመጀመሪያ 5 ወራት (እስከ ህዳር 30/2018 . ድረስ) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዲጂታል የሙስና መረጃ (ጥቆማ) መቀበያ ሥርዓት እና በሌሎች አማራጮች ከቀረቡ ጥቆማዎች ውስጥ 54 አመራርና ሠራተኞች ጥፋተኛ መሆናቸው ተረጋግጦ እርምጃ ተወስዷል።

ተቋሙ ተግባራዊ ባደረገው የዲጂታል ሙስና ጥቆማ ማቅረቢያ በቀረቡት ጥቆማዎች መሠረት እርምጃ ከተወሰደባቸው ሠራተኞች መካከል 10 የፅሁፍ፣ 37 የደመወዝ፣ 2 ከቦታ የማንሳት፣ 5 ስንብት በድምሩ 54 ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱን ተቋሙ አስታውቋል።

እርምጃው የጥቆማ መቀበያ ስርዓቱ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ፣ ደንበኞች የሚሰጡት ጥቆማ ዋጋ ያለው መሆኑን እና የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ለመታገል ተቋሙ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ስለመሆኑ ተገልጿል።

ተቋሙ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግርና ብልሹ አሰራሮችን ለመታገል እና እርምጃ ለመውሰድ ወደፊትም በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አረጋግጧል።

ተገልጋዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት መሰል ችግሮችን ሲመለከቱ ለዚሁ በተዘጋጀው ዘመናዊ የሞባይል መተግበሪያ ወይም በድረ-ገፅ (www.eeuethics.et) በመጠቆም የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል።

#EBC #ebcdotstream #EEU #ethicaltransgressions #administrativemeasures