ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ለመጡት የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገወዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ለይፋዊ ጉብኝት በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል” ብለዋል።
“የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል እያደገ የመጣውን ትስስር የሚያመለክት ሲሆን ውይይቶቻችን በጋራ የቅድሚያ ጉዳዮቻችን ላይ ትብብሮቻችንን የበለጠ የምናጠናክርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው።” ሲሉም አክለዋል።