Search

በጁገል የሚከናወነው ዕድሳት ቅርሱን በዘላቂነት ለትውልድ ለማሸጋገር ያስችላል - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

ማክሰኞ ታኅሣሥ 07, 2018 34

የጁገል ቅርስን ዘላቂ በሆነ መልኩ በማደስ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ እየተሠራ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ 4ኛውን ዙር የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ሥራ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በዚህ ወቅትም የልማት ሥራውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ጥራት፣ ፍጥነትና ፈጠራ በታከለበት ሁኔታ እየተሰራ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
ሥራው የድንጋይ ንጣፍ፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የመንገድ መብራቶች እና የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓትን ያካተተ መሆኑም ተገልጿል።
ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በጁገል ቅርስ ዙሪያ እና በተለያዩ ቦታዎች እየተከናወነ የሚገኘው የዕድሳትና የመልሶ ልማት ሥራ፤ ቅርሱን ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር የላቀ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።
 
በቴዎድሮስ ታደሰ