የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመላ ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያንም ጎብኝተዋል።
የናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት የኢትዮዽያና ህንድን የቆየ ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የሚያሸጋግር ነው።
ኢትዮጵያ እና ህንድ በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በባህል ግንኙነት የረጅም ጊዜ ታሪክ አላቸው።