Search

በአንድነት እና በትብብር በመሥራት ትላልቅ ግቦችን ማሳካት ይቻላል - ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ

ረቡዕ ታኅሣሥ 08, 2018 68

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል።

ስለ አንድነት እና ትብብር አስፈላጊነት ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ፤ አንድነት እና ትብብር ጥንካሬን ይሰጣሉ ሲሉ ገልጸዋል።

"ድር ቢያብር፣ አንበሳ ያስር" የሚለው የኢትዮጵያውያን ምሳሌያዊ አነጋገር አንድነት እና ትብብር ምን ያህል ትልቅ አቅም እንዳላቸው ማሳያ ነው ብለዋል።

አያይዘውም፥ በአንድነት እናትብብር በመሥራት ትላልቅ ግቦችን ማሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያላትን የረጅም ጊዜ ታሪክ፣ ባህል እና የአመራር ሚና አንስተው፤ ሕንድ እና ኢትዮጵያ ጠንካራ የስልጣኔ ትስስር አላቸው ብለዋል።

ሁለቱን ሀገራት በሰላም እና በልማት ዙሪያ  የቆየ አጋነት እንዳላቸው ጠቅሰው፤  ሕንድ በንግድ፣ ቴክኖሎጂ፣ ትምህርት፣ምግብ ዋስትና እና የጤና አገልግሎት ዘርፎች የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በቢታንያ ሲሳይ

#EBCdotstream #Ethiopia #India #NarendraModi