የደሴ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ እየታየ ያለውን የህዝብ የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት 5 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ግዥ በመፈፀም ስራ ለማስጀመር ርክክብ አድርጓል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙዔል ሞላልኝ፤ በነዳጅ እጥረት ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳይስተጓጎል ባለ ብዙ አማራጭ ትራንስፖርት መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
ደሴ ከተማን ለኗዋሪዎቿ ምቹ፣ ፍፁም ሰላማዊ፣ የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ስሉጥ ከተማ ለማድረግ በትጋት እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
የመደመር መንግስት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ሳሙኤል፤ የህዝባችንን አቅም በመጠቀም ከተማችንን ስልጡን እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ በትጋት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ለደሴ ከተማ የሚመጥን ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት በቅርቡ የሚጀምሩት የኤሌክትሪክ ባሶች የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማዘመን እንደሚያግዙ ገልጸዋል።
አውቶብሶቹ በቅርቡ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ተመድበው አገልግሎት እንደሚሰጡ የደሴ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ዛሬ የተረከባቸው በኤሌክትሪክ የሚሠሩ አውቶብሶች በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የተገጣጠሙ መሆናቸው ተመላክቷል።
#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #DessieCity #electricbuses