Search

የተፈጥሮ ፀጋን ወደ ልማት እና ቱሪዝም የመቀየር ጥበብ በሀምበሪቾ 777

ዓርብ ጥር 08, 2018 569

ሀምበሪቾ 777 ላይ ስንወጣ የምናየው እጅግ ማራኪ ተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን፣ የተፈጥሮ ፀጋን ወደ ልማት እና ቱሪዝም የመቀየር ጥበብን ጭምር ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የፓርቲው ዋና /ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

አቶ አደም ፋራህ ባለፉት 3 ቀናት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ የነበረው 2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

መድረኩ ካለፉት ስኬቶች ልምድ የተቀሰመበት፣ ድክመቶች በብልፅግና እሳቤ የተመዘኑበት እናቀጣይ ፓርቲውን ይበልጥ የሚያጠናክሩ እና የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን በቁርጠኝነት ለመፈፀም አቅጣጫ የተቀመጠበት እንደነበር ጠቁመዋል።

መድረኩን ካጠቃለሉ በኋላ በከምባታ ዞን ያደረጉት ጉብኝት የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር ልማት መሬት ላይ ወርዶ ፍሬ ማፍራቱን በተግባር የታዘቡበት መሆኑንም ገልጸዋል።

የከምባታ ሕዝብ የሚታወቅበት የታታሪነት፣ትምህርት እና ሥራ ወዳድነት እንዲሁም የእንግዳ ተቀባይነት እሴት ለዛሬው ስኬታችን ትልቅ መሠረት መሆኑን ዳግም አረጋግጠናል ሲሉም ለሕዝቡ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ሀምበሪቾ 777 የኅብረተሰቡን ተሳትፎ እና የመንግሥትን አመራር በማቀናጀት እንዴት ትልልቅ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል አቶ አደም ፋራህ።

በተለይም የባለራዕዩ ወጣት አብነት መንደር ጉብኝታችን፣ የኢትዮጵያዊ ብልፅግና ትርጉም በቤተሰብ እና በአካባቢ ደረጃ እንዴት እንደሚገለጽ በተጨባጭ ያሳየ ትልቅ የልምድ መጋሪያ ሆኖናል ሲሉ ገልጸዋል።

በአካባቢው ያየናቸው የልማት ሥራዎች እና የተመዘገቡት ውጤቶች የሚያረጋግጡት አንድ ትልቅ እውነት አለ ያሉት አቶ አደም ፋራህ፣ "የተቀናጀ አመራር እና የሕዝብ ንቅናቄ ካለ የማይታለፍ ተራራ፣ የማይፈታ የልማት ጥያቄ የለም!" ሲሉ አረጋግጠዋል።

የከምባታ ዞን አመራሮች እና መላው የዞኑ ሕዝብ ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል እና እያሳያዩት ላለው የልማት ቁርጠኝነትም ምስጋና አቅርበዋል።

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #hambaricho777 #prosperity