Search

በታክስና ጉምሩክ ሕጎች ላይ የተደረገው ማሻሻያ የገቢ መጠንን በእጅጉ አሳድጎታል - የገቢዎች ሚኒስቴር

ሓሙስ ጥር 21, 2018 156

በኢትዮጵያ በታክስና ጉምሩክ ሕጎች ላይ የተደረገው ማሻሻያ የገቢ መጠንን በእጅጉ ማሳደጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህ የተባለው የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉሙሩክ ኮሚሽን የ2018 የመጀመሪያ 6 ወራት ዋና ዋና እና የሪፎርም ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማ በተካሄደበት መድረክ ነው።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ፥ በተከናወኑ በርካታ ማሻሻያዎችም እስከ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 760 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

ይህም ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት አንፃር እጅግ ከፍተኛ ገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህ ውጤት ከሕግ ማሻሻያው ባሻገር ተጨማሪ የአገልግሎት ማዕከላትን ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መደረጉ፣ ብሎም ለተቋሙ የሰው ኃይል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በስፋት መሰጠቱ ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል።

በዚህም በጀት ዓመቱ የገቢዎች ሚኒስቴር ገቢ በመሰብሰብ ረገድ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትሪሊዮን የተሸጋገረበት መሆኑ በመድረኩ ተጠቅሷል።

በቢሾፍቱ እየተካሄደ ያለው ግምገማ እስከ ጥር 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይዘልቃል።

በሳምሶን በላይ

#EBCDotstream #Ethiopia #Revenue #Tax