Search

የአህጉሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአፍሪካውያን የጋራ ቤት አዲስ አበባ ...

ማክሰኞ የካቲት 03, 2018 36

በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና በ48ኛው የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የጂቡቲ፣ የጊኒ፣ የሌሶቶ፣ የቻድ እና የሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።
በዚህም መሠረት፦
 
• የጂቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኡመር፣
• የጊኒ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሪሳንዳ ኩያቴ፣
• የሌሶቶው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጆን ምፖትጆአና፣
• የቻዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላዬ ሳብሬ ፋዱል እና
• የሞሮኮው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ
• የጋቦን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪ-ኤዲት ታሲላ ዬ ዱምቤኔኒ፣
• የሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቪዬ ጄ.ፒ. ንዱሁንጊሬሄ፣
• የጋምቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴሪንግ ሞዱ ንጂ እና
• የኢኳቶሪያል ጊኒው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሞን ኦዮኖ ኢሶኖ አንጉዌ አዲስ አበባ የገቡት በዚሁ ሳምንት በሚካሄዱት አህጉራዊ ስብሰባዎች ላይ ለመሳተፍ ነው።
 
ሚኒስትሮቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት (የሚኒስትሮች ምክር ቤት) 48ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ የሚያካሂድ ሲሆን፤ ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችንም ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
 
በሳምሶን በላይ