Search

የፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ ለዒድ አል-ፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ዓርብ መጋቢት 11, 2018 41

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ ለ1447ኛው ዒድ አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክት፤ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለዒድ አል-ፈጥር በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።