Search

የላይቤሪያው ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሓሙስ ሚያዝያ 08, 2018 98

የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ፕሬዝደንቱ በኢትዮጵያ ባለፉት ቀናት ያደረጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ማለዳ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ሽኝት አድርገውላቸዋል።
ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ግዛት ያልተገዙ፣ ለአኅጉሪቱ ነፃነትና አንድነት ድምፅ በመሆን ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው።
የአሁኑ የፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የሥራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያጠናክራል።
በአስማረ ብርሃኑ