Search

ሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር የሉዓላዊነት ጥቃት አካል ነው - ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ነሐሴ 06, 2017 176

ኢትዮጵያሰተኛ መረጃን እና የጥላቻ ንግግርን የብሔራዊ ጥቅም እና የሉዓላዊነት ጥቃት አካል አድርጋ ነው የምትመለከተው ሲሉ ቢቂላ ሁሪሳ (/ር) ገለጹ።

ይህን ጥቃት ለማምከን የሚደረገው የተቀናጀ ትግልም በዚያው ልክ ከፍ ያለ ነው ብለዋል በጠቅላይ ሚኒስትር /ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊው ቢቂላ ሁሪሳ (/ር) ከኢቢሲ ኤፍኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ።

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር እንዲሁም በቀጣናው ትክክለኛ እና ፍትሐዊ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመናዋን ለመጎናፀፍ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ አቅደው የሚሰሩ  ጠላቶች አሁንም አሉ ሲሉ / ቢቂላ ተናግረዋል።

በትጥቅ ትግል እና በሌሎች መንገዶች ያልተሳካላቸውን ተልዕኮ በሐሰተኛ መረጃ እና በጥላቻ ንግግር በኩል የህዝቦችን መተማመን በመሸርሸር ወደ ግጭት ለማስገባት የሚደረግ ሙከራ በመሆኑ እንደ ሉዓላዊነት ጥቃት ይወሰዳል ብለዋል።

ዜጎችም ጉዳዩን ከኢትዮጵያ ክብር እና ሉዓላዊነት አንፃር በማየትሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግርን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ / ቢቂላ ጥሪ አቅርበዋል።

በቤተልሔም ገረመው

#ኢቢሲ #ኢቢሲዶትስትሪም #ሐሰተኛመረጃ #የጥላቻንግግር