Search

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ተካሂዷል - የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን

ረቡዕ ግንቦት 26, 2018 41

ፌዴሬሽኑ እንደ አንድ የሲቪል ድርጅት በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫውን ፍትሐዊነት፣ ተዓማኒነት እና አካታችነት ሲከታተል ነበር።

ከምርጫ ጣቢያዎች መከፈት ቀደም ብሎ ጀምሮ በምርጫ ጣቢያዎች የታየው የመራጮች ሰልፍ፣ የምርጫውን ፍትሐዊነት ያሳየ ነው ብሏል።

የምርጫ ቁሳቁስ እጥረት ያልተከሰተበት፣ የምርጫ አስፈፃሚዎች ግዴታቸውን በአግባቡ የተወጡበት እና መራጩ ማኅበረሰብም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምፅ የሰጠበት እንደሆነ መታዘቡን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

የፀጥታ አካላት፣ የምርጫ አስፈፃሚ እና በጎ ፈቃደኞች ሁሉ በቅንጅት ተናበው መስራታቸው የምርጫውን ሂደት ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ማስቻሉን ጠቁመዋል።

በተለይ ወጣቱ ክፍል ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ባሉ በሁሉም የምርጫ ሂደቶች ውስጥ ካለ ምንም እንከን በበጎ ፈቃድ በመሳተፍ ለሀገረ መንግሥት ምስረታ ያለውን ሚና አሳይቷል።

ፌዴሬሽኑ ሁሉም የምርጫ ሂደቶች ፍትሐዊ፣ አካታች እና ነፃ መሆናቸውን አስታውቋል።

በድህረ ምርጫ ሂደቶች ውስጥም ወጣቱ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በተለይ የተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ሌሎች በምርጫው ሂደት የተካፈሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ትልቅ መሆኑን ፌዴሬሽን ጠቁሟል፡፡

ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚወጡ ውጤቶችን በፀጋ በመቀል ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የራሳቸውን አበርክቶ እንዲያደርጉም ተጠይቋል።

በሳምሶን ገድሉ