Search

ቼልሲ ሞርጋን ሮጀርስን በ117 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከአስቶን ቪላ ጋር ተስማማ

ቅዳሜ ሐምሌ 11, 2018 79

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛውዩን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ሞርጋን ሮጀርስን በ117 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ለማስፈረም ከአስቶን ቪላ ጋር በቃላት ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ይህ ዝውውር ከተጠናቀቀ፣ ማንቸስተር ሲቲ ኤሊዮት አንደርሰንን ከኖቲንግሃም ፎረስት በ116 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም የደረሰበትን ስምምነት በመብለጥ አዲስ የእንግሊዝ የዝውውር ሪከርድ የሚያስመዘግብ ይሆናል ተብሏል።

በዘንድሮው የክረምት የዝውውር መስኮት የአርሰናል ዋነኛ የፊት መስመር ኢላማ የነበረው ይኸው አጥቂ፤ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዋንጫው ላይ ከፈረንሳይ ጋር ለሚደረገው የደረጃ ማጠቃለያ ጨዋታ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: