Search

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥራ አፈጻጸም ዋና ዋና ነጥቦች፦

ሓሙስ ነሐሴ 07, 2018 67

 

➡ የሥራ አፈጻጸም ስኬት፡ የኮሚሽኑ የምክክር ሂደት ባቀደውና በተጠበቀው ልክ በስኬት እየተካሄደ ሲሆን፣ እስካሁንም ከጠቅላላ ሥራው ሦስት አራተኛውን (75%) ማጠናቀቅ ችሏል።

➡ የምክክር ቡድኖች ስምምነት፡ እያንዳንዳቸው 500 ተመካካሪዎችን ያቀፉ 8 የምክክር ቡድኖች ውይይቶችን በማካሄድ፣ በአብዛኛዎቹ ምክረ-ሀሳቦች ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ፊርማቸውን አኑረዋል።

➡ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት፡ በውይይቱ ወቅት ያጋጠሙ የሀሳብ ልዩነቶችና አለመግባባቶች ተመካካሪዎቹ እርስ በእርስ በመደማመጥ ወደ አንድ የጋራ አማካይ ሀሳብ ማምጣት መቻላቸው የሀገራዊ ምክክሩን አስፈላጊነት ይበልጥ ያረጋገጠ ሆኗል።

➡ የምክረ-ሀሳቦች ማጣጣም ሥራ፡ ስምንቱ ቡድኖች ያዘጋጇቸውንና የተስማሙባቸውን ምክረ-ሀሳቦች የሚያጣጥም፣ በሚቀርቡ ሀሳቦች መካከል መጣረስ እንዳይኖር ጥንቃቄ የሚያደርግና ለጠቅላላ ሀሳቦቹ ወጥነት የሚፈጥር ልዩ ቡድን ተቋቁሟል።

➡ የቅሬታ አፈታት ሥርዓት፡ ከግለሰቦች፣ ከቡድኖችና ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚቀርቡ ማናቸውንም ቅሬታዎች ኮሚሽኑ በተዘረጋው የቅሬታ መፍቻ ሥነ-ሥርዓት መሠረት እየተቀበለና እያጠና ውሳኔ በመስጠት ላይ ይገኛል።

➡ ቀጣይ ምዕራፍ፡ ለረጅም ጊዜ ጥረት ሲደረግበት የቆየው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ውጤታማነት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚበሰርበት ቀጣዩ ምዕራፍ በቅርቡ ይጀምራል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: