በኢትዮጵያ በ70 ከተሞች እየተተገበረ ያለው የኮሪደር ልማት ከተሞችን ለኑሮ፣ ለሥራ እና ለመዝናኛ ምቹ በማድረግ መሠረታዊ ለውጥ እንዲመጣ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ተናገሩ።
ከለውጡ በፊት 74 በመቶ የነበረውን ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ የኢትዮጵያ ከተሞች መጠን ከለውጡ ወዲህ ወደ 52 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል ብለዋል ሚኒስትሯ።
በአዲስ አበባ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ወደ ክልሎች በማስፋት ከተሞች መኖሪያ ብቻ ሳይሆኑ ማምረቻ እንዲሆኑ በተከናወነው ተግባር የሥራ ዕድል መፍጠር እንዲሁም የሥራ ባህልን መቀየር መቻሉንም ገልፀዋል።
የኮሪደር ልማት የሥነ-ውበት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የልማት እሳቤ ጭምር ነው፤ በዚህም የከተሞችን የአረንጓዴ ሽፋን በማሳደግ እና መሠረተ ልማትን በማስፋት ንፁህ፣ ውብና ማራኪ ለማድረግ፤ የነዋሪዎችን የአኗኗር ዘይቤ ለመቀየር እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆኑ ለማስቻል እየተሠራ ነው ብለዋል።
በ70 ከተሞች እየተተገበረ ያለው የኮሪደር ልማቱ ለበርካቶች የሥራ ዕድልን የፈጠረ፤ ዜጎች ቀን ከሌት፣ ቁር ከሐሩር ሳይመርጡ የሥራ ባህልን እንዲያዳብሩ ያስቻለ ትልቅ እሳቤ ነው ብለዋል የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ።
በላሉ ኢታላ
##ኢቢሲዶትስትሪም #ኮሪደር_ልማት #ሰባ_ከተሞች