Search

የኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ፡ በመደመር እሳቤ የታነጸው ስትራቴጂያዊ ከፍታ

እሑድ መስከረም 17, 2019 116

ታሪክ በባለቤቶቹ ላብ፣ ደም እና ቁርጠኝነት የሚጻፍ እንጂ በአጋጣሚ የሚሰጥ ስጦታ አይደለም።

ትናንት የገጠሟትን ፈተናዎች እና የውጭ ጫናዎች በጽናት ያከሸፈችው ኢትዮጵያ ዛሬ በሁለንተናዊ አቅሟ ተነስታ የብልጽግናን አዲስ ምዕራፍ በመደመር እሳቤ እና በኢኮኖሚ ነፃነት እያረጋገጠች ትገኛለች።

የኢትዮጵያን አጠቃላይ ገጽታ የቀየረው እና የነገን ብሩህ ተስፋ ያበሰረው ይህ ጊዜ እውነተኛ የማንሰራራት እና የከፍታ ዘመን ነው።

ይህ ምዕራፍ የህልውና መረጋገጥ ብቻ ሳይሆን የሉዓላዊነት፣ የፈጣን ዕድገት እና የሁለንተናዊ ትራንስፎርሜሽን ማሳያ ነው።

የዚህ የማንሰራራት ዘመን ዋነኛ መገለጫ የሆነው የውጭ ግንኙነት ቁመናችን፣ የሀገራችንን ስትራቴጂያዊ ልዕልና በግልጽ ያሳያል።

የሀገር ግንባታ ውስጣዊ የልማት ሥራዎችን በማጠናቀቅ ብቻ የሚወሰን አይደለም፤ በመደመር መንፈስ ልዩነቶቻችንን አስተካክለን፣ ከቀጣናው እስከ ዓለም አቀፍ መድረኮች ጠንካራ አህጉራዊ ተሰሚነት እና የዲፕሎማሲ ክብደት መገንባትን የሚጠይቅ ግዙፍ የትውልድ አደራ ነው።

ዛሬ ኢትዮጵያ በውስጥ አቅሟ ተማምና "ኢትዮጵያ ትችላለች!" የሚለውን መርህ በተግባር እያሳየች ነው።

በዓለም አቀፍ መድረኮች በተለይም በብሪክስ ጉባኤዎች እና ማዕቀፎች ውስጥ ሀገራችን እያሳየች ያለችው ንቁ ተሳትፎ፣ የጂኦ-ፖለቲካዊ ክብደቷን እና የውሳኔ ሰጪነት አቅሟን ከፍ ያደረገ ታሪካዊ እርምጃ ሆኗል።

ይህ የዲፕሎማሲ ስኬት በጠንካራ የመሰረተ ልማት፣ የኃይል እና የትራንስፖርት ትስስር የታገዘ ነው።

የአፍሪካ የአቪዬሽን ማዕከልነቷን በአስተማማኝ ሁኔታ ማስቀጠሏ እንዲሁም አሁን ላይ በይፋ ተመርቆ ሙሉ አገልግሎት መስጠት በጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አማካኝነት ለጎረቤት ሀገራት የመብራት ምንጭ በመሆን ቀጣናውን በኃይል ማስተሳሰሯ፣ ኢትዮጵያን የሰፊው አህጉር የንግድ፣ የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ማዕከል አድርጓታል።

ከዚህም በተጨማሪ የኢኮኖሚ እምቅ አቅሞችን ከማስተሳሰር እና የጋራ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንፃር የሚከናወኑ ሁለገብ ሥራዎች ስትራቴጂያዊ የጂኦ-ፖለቲካ አቀማመጣችንን ይበልጥ አጠናክረውታል።

የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ጉዞ ዛሬ ላይ ተደማጭ እና የነገውን አህጉራዊ የምጣኔ ሀብት እና የፖለቲካ ምህዳር በባለቤትነት የሚቀርጽ ቁመና ላይ ደርሷል።

ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥት መርሕ እና በብሔራዊ ጥቅሟ ላይ በተመሰረተ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂ፣ የማንሰራራት ዘመኗን በብሩህ ተስፋ እያጸናች እና በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላትን ድምጽ ይበልጥ ከፍ እያደረገች ትቀጥላለች፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ሁልጊዜም ትችላለች።

በሔዋን ጌታቸው

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: