የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብት እና መስህቦች ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች በማስተዋወቅ እና የኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማሳደግ የሀገራችንን የቱሪዝም ገጽታ ለማጠናከር ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች እና የንግድ መድረኮች ለማስተዋወቂያ ሥራ እየዋሉ ነው።
የአፍሪካ የጤና እንክብካቤ ማምረቻ ንግድ ትርዒት እና ኮንፈረንስ (AHMTEC) በስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ ሲሆን፣ መድረኩ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብት እና መስህቦች ለዓለም አቀፍ ተሳታፊዎች ለማስተዋወቅ ዕድል ፈጥሯል።
የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር በእነዚህ መድረኮች የሚሳተፉ ዓለም አቀፍ እንግዶች በኢትዮጵያ ቆይታቸው የአዲስ አበባን እና አካባቢዋን የቱሪዝም መስህቦች እንዲጎበኙ የማስተዋወቅ ሥራዎችን እያከናወነ ነው።
በተጨማሪም በቅርቡ የተገነቡ እና የታደሱ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች በማስተዋወቅ፣ የሀገራችንን ልዩ የተፈጥሮ፣ የባህል እና የታሪክ ሀብቶች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ ነው።
እንደ AHMTEC ያሉ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ከሙያዊ ውይይት እና ከንግድ ልውውጥ ባሻገር፣ የሀገርን ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅ፣ የውጭ ጎብኚዎችን እና ባለሀብቶችን ለመሳብ እንዲሁም የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና አላቸው።
ይህም ለሆቴል እና ለእንግዳ ተቀባይነት ዘርፍ ዕድገት፣ ለአገልግሎት ዘርፉ መነቃቃት እና ለሀገራችን የቱሪዝም ኢኮኖሚ መጎልበት ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ትናንት የጀመረው የአፍሪካ የጤና እንክብካቤ ማምረቻ ንግድ ትርዒት እና ኮንፈረንስ (AHMTEC) እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: