የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቀጨኔ–ጊዮን–ባምቢስ እስከ ሰላም መንገድ ድረስ የተገነባውን ዘመናዊ እና ማራኪ የወንዝ ዳርቻ ልማት ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች በምሽት ውበቱ እንዲጎበኙት ጥሪ አቅርበዋል።
ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት፣ “ወዳጆቻችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን ይዛችሁ ኑ፤ ከዕለት ድካም እረፍት ውሰዱ፣ በፅዱ እና በውብ አካባቢው ንፁህ አየር ተቀበሉ፣ መንፈሳችሁንም አድሱ! አዲስ አበባ ውበቷን ለማየት ብቻ ሳይሆን፣ ለመኖርና ለመደሰትም ጎራ በሉ!” ሲሉ ጋብዘዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: