Search

የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር ) ከዓለም ባንክ ቡድን ዋና ዳይሬክተር እና ቺፍ ኖውሌጅ ኦፊሰር ጋር ተወያዩ

ሓሙስ ኅዳር 03, 2019 104

በአንታሊያ፣ ቱርክዬ እየተካሄደ ካለው የCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን፣ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር )፣ ከዓለም ባንክ ቡድን ዋና ዳይሬክተር እና ቺፍ ኖውሌጅ ኦፊሰር (Chief Knowledge Officer) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም ከCOP32 ዝግጅት አንጻር በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ትብብር ስለማጠናከር ያካተተ ሲሆን፣ በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (ኢ-ሞቢሊቲ)፣ በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ተግባራዊ አፈጻጸም እንዲሁም ከካርቦን ክሬዲት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: