ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ አትሌት ማርታ ዓለማየሁ፣ የዓለም አትሌቲክስ ባዘጋጀው የ2026 የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ ሴት ኮከብ ወይም 'ራይዚንግ ስታር' ምርጫ የመጨረሻ 3 ዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተች።
የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ ይፋ ባደረገው ዝርዝር ዕጩዎቹ ዘንድሮ ከ20 ዓመት በታች ውድድሮች ላይ ላሳዩት ድንቅ ብቃት እውቅና ለመስጠት መመረጣቸውን አስታውቋል።
ማርታ ለዚህ ዓለም አቀፍ ክብር የበቃችው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የሀገር አቋራጭ ሻምፒዮንነት ክብሯን ማስጠበቅ በመቻሏ እንዲሁም በ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ 14 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ በመግባት በታሪክ 3ኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገቧ ነው።
በዚህ ምርጫ ከማርታ ጋር አሜሪካዊቷ የ100 እና 200 ሜትር አጭር ርቀት ሯጭ ሚያ ማክስዌል እና ቻይናዊቷ የጦር ውርወራ ክብረወሰን ባለቤት ያን ዚዪ የጨረሻ ዕጩ ሆነው ተካተዋል።
አሸናፊዋ ሕዳር 20 ሞናኮ ላይ በሚዘጋጀው የዓለም አትሌቲክስ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የምትታወቅ ይሆናል።
በእሱባለው ተሾመ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: