Search

በአዲስ አበባ በ21 ሳይቶች 100 ሺህ ቤቶችን እየገነባን ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዓርብ ኅዳር 04, 2019 118

ከጉባ ብስራቶች አንዱ እንደ ሀገር በአምስት ዓመታት ውስጥ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለዜጎቻችን ለማስረከብ የገባነው ቃል ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ እንደ አዲስ አበባ በ21 ሳይቶች 100 ሺህ ቤቶችን እየገነባን ነው ብለዋል።

እነዚህም 50 ሺህ በከተማው በጀት፣ 50 ሺህ ደግሞ በመንግሥት–የግል አጋርነት እና በማኅበራት እየተገነቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዛሬም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በቱሉ ዲምቱ 33 ብሎኮችን እና በአዲስ ከተማ ቅጠል ተራ 9 ብሎኮችን ጎብኝተን ጥሩ አፈፃፀም ላይ መሆናቸውን ተመልክተናል ብለዋል።

የሕዝባችንን የቤት ጫና ማቃለል ለእኛ የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን፣ አደራና ኃላፊነት በመሆኑ 24/7 ተግተን እንሰራለን ሲሉም አመላክተዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: