ለ197ኛ ጊዜ የተደረገው የማንቹሪያን ደርቢ በማንችስተር ሲቲ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ኧርሊንግ ብሮውት ሃላንድ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
በኢትሀድ በተደረገው የ4ኛ ሳምንት ጨዋታ ፊል ፎደን ደግሞ አንዷን ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል፡፡
ሃላንድ ዩናይትድ ላይ 8ኛ ግቡን ሲያቆጥር ፊል ፎደን 7ኛ የደርቢ ግቡን ከመረብ አሳርፏል፡፡
ማንችስተር ሲቲ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡
የፔፕ ጋርዲዮላ ስብስብ በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ከአርሰናል የሚገናኝም ይሆናል፡፡
በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ ከቼልሲ ይጫወታል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ