ኢሬቻ የወንድማማች በዓል መሆኑ በተግባር የታየበት ነው ሲሉ የሆረ ሀርሰዴ ታዳሚዎች ገለጹ።
ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመሰባሰብ በዓሉ በአብሮነት እና በፍቅር መከበሩን ገልጸዋል።
ሁሉም በየራሱ ቀለም እና መልክ ተውቦ፣ አምሮ እና ደምቆ የሚታይበት እንደሆነም አንስተዋል።
በዓሉ ስለ እርቅ ስለ ሰላም፣ ስለ አንድነት አብዝቶ የሚሰበክበት ስለ መሆኑም ነው ያነሱት።
የምስጋና በዓል የሆነው ኢሬቻ ከዓመት ዓመት እየደመቀ እና እየተዋበ እንደመጣም ነው የጠቀሱት።
የሁሉም ኢትዮጵያውያን የሆነውን ይህን በዓል፣ እሴት እና ትውፊቱን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በዓሉ የኢትዮጵያን ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አጉልቶ ያሳየ እንደሆነም ታዳሚዎቹ ጠቅሰዋል።
በሜሮን ንብረት
#EBCdotstream #Ethiopia #Irreecha #HoraHarsade