የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ከተማ “ኢሬቻ ለሀገር ማንሠራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በድምቀት ተከብሯል።
በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የመጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ታድመዋል።