የ"Pulse of Africa" ሚዲያ ሥራ መጀመር አፍሪካን በአሉታዊ ገጽታ የማቅረብ ሥራን ለመመከት ብሎም የራሳችንን ትርክት በራሳችን የመቅረጽ ተግባራችንን የምናፀናበት ጠቃሚ ርምጃ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።
ምንም እንኳ አፍሪካ ሰፊ እና እምቅ ሀብት ያላት አኅጉር ብትሆንም አብዛኛውን ጊዜ እንደ አነስተኛ እና አቅመቢስ ተደርጋ ትሳላለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በዚህ የተነሳ ነው አነስተኛ ግን እጅግ ትርጉም ያለው የPulse of Africa ጅማሮ በመጪዎቹ ጊዜያት ከፍ ወዳለ መሪ አኅጉራዊ ሚዲያ የማደግ መንገድ እጅግ ጠቃሚ የሚሆነው ብለዋል።
አፍሪካ ዐቢይ የኢንደስትሪ ማዕከል እና የዓለም ቁልፍ ሚና ተጫዋች የመሆን መንገድ ላይ በማያጠራጥር መንገድ እየተጓዘች ትገኛለች ሲሉ አመላክተዋል።
የPulse of Africa መቋቋም ወደፊት የመመልከት ርምጃ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዓለም መድረክ ጠንካራ እና ቱባ የአፍሪካ ድምፅ የማሰማት መሠረትም ነው ብለዋል።