ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "Pulse of Africa" የተሰኘ የፓን አፍሪካ ሚዲያ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ መገኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ሚዲያው ጠቅላይ ሚኒስትር እ.ኤ.አ. በ2022 በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአፍሪካን እይታ እና ትርክት የሚያንፀባርቅ የአኅጉራዊ ሚዲያን አስፈላጊነት አስመልክተው ያቀረቡትን ጥሪ በመመርኮዝ የተመሠረተ መሆኑ ተገልጿል።
Pulse of Africa የአፍሪካን ድምፆች የሚያጎላ፣ ቀጠናዊ ትስስርን የሚያጠናክር እና አኅጉራዊ ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና ሕልሞችን በአፍሪካዊ እይታ የሚገልጥ ሚዲያ የመሆን አላማ እንዳለው ተመላክቷል።