Search

በመጀመሪያ የሙከራ እርሻ ጥሩ ምርት የተገኘበት የሱፍ ልማት በአፋር ክልል

እሑድ ኅዳር 28, 2018 70

በአፋር ክልል፣ አሚበራ ወረዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሙከራ የለማው የሱፍ ሰብል ምርት እየተሰበሰበ ይገኛል።

በወረዳው ለመጀመሪያ ጊዜ ለሙከራ ከለማው 500 ሄክታር የሱፍ እርሻ ጥሩ ምርት መገኘቱን የመካካለኛው አሚበራ እርሻ ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኩራባቸው ዘለቀ ገልጸዋል።

5 ሺ ኩንታል የሱፍ ምርት መሰብሰቡን የገለጹት አቶ ኩራባቸው፤ የሱፍ ልማቱ ከ400 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢ ነዋሪዎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል። 

ከሙከራ ልማቱ የተገኘው የሱፍ ምርት ጥሩ በመሆኑ በቀጣይ በስፋት ለማልማት እንደሚሠራ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።

የምርት አሰባሰብ ሂደቱን በቦታው ተገኝተው የተመለከቱት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አሚን መሐመድ፥ በክልሉ ለሱፍ ምርት መስፋፋት በተሰጠው ትኩረት ከአሚበራ በተጨማሪ በዱብቲ ወረዳም ከ500 ሄክታር በላይ ሱፍ በኢንቨስትመንት እየለማ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም በክልሉ በሱፍ እና  በሌሎች የግብርና ልማት ሥራዎች  ላይ ኢንቨስትመንትን በማስፋት በትኩረት እንደሚሠራ አቶ አሚን አመላክተዋል።

በሁሴን መሐመድ

#ebcdotstream #afar agriculture #sunflower