18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓለማ ቀን በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ሚስዮኖች ተከብሯል፡፡
በጀርመን በርሊን፣ በቤልጂየም ብራሰልስ፣ በደቡብ ኮሪያ ሴኡል፣ በቱርክ አንካራ፣ በኬንያ ናይሮቢ፣ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ እና በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች አምባሳደሮች፣ ሠራተኞች እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከብሯል፡፡
በተለያዩ ሀገራት በተካሄደው የሰንደቅ አላማ ቀን ክብረ በዓል ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር የሰንደቅ አላማ መስቀል ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
በመሀመድ ፊጣሞ
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #FlagDay