Search

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን ደብዳቤ ተቀበሉ

ማክሰኞ ጥቅምት 04, 2018 43

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት የተቀበሏቸው አምባሳደሮችም የሞሪታኒያ፣ የካዛኪስታን፣ የቫቲካን፣ የባንግላዴሽ፣ የአረብ ሊግ፣ የኢንዶኒዢያ፣ የሰርቢያ፣ የስዊዲን፣ የካናዳ፣ የስዊዘርላንድ፣ የግብፅ፣ የሀንጋሪ፣ የሳንማሪኖ እና የቱርኪሚስታን ናቸው።
የሀገራቱ አምባሳደሮች በሰላምና ፀጥታ በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ፣ በማዕድን ልማት፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎችም ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
 
በሌላ በኩልም ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በጂቡቲ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ለተሾሙት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
 
በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተከናወነው በዚሁ መርሃ ግብር ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ለገሰ ቱሉ ሀገራቸውን የሚያኮራ ተግባር እንደሚያከናውኑ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል ታየ አፅቀ ሥላሴ።
በይመር አደም