Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የወልመል ወንዝ መስኖ ልማት ፕሮጀክትን መረቁ

ቅዳሜ ጥቅምት 08, 2018 81

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባሌ ዞን፣ ደሎ መና ወረዳ በመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አማካኝነት የተጀመረውን የወልመል ወንዝ መስኖ ልማት ፕሮጀክትን መርቀዋል።

ፕሮጀክቱ የወልመል ወንዝን በመስኖ በሚገባ በመጠቀም የግብርና ምርታማነትን በማላቅ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወነ መሆኑም ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ ዘላቂ የገጸምድር የመስኖ ሥርዓት በመገንባት፤ የግብርና ሥራው ለዘመናት በዝናብ ውኃ ላይ ተመስርቶ የነበረውን የአካባቢውን ሕዝብ ዘላቂ የኑሮ ዘዴ ለማጎናፀፍ ታልሞም መከናወኑ ነው የተጠቆመው።

ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት 20ሺህ ለሚሆኑ አርሶአደሮች ለሚያገለግል 9ሺህ 687 ገደማ ሄክታር የእርሻ መሬት አስተማማኝ የመስኖ አቅርቦት ይኖረዋልም ነው የተባለው።

ይኽም የግብርና ምርታማነትን የሚያሳደግ፣ ለድርቅ የማይበገር ከባቢን የሚፈጥር ብሎም በማኅበረሰቡ አዳዲስ የሥራ እድል የሚፈጥር ይሆናል።

ከነዚህ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ባሻገር የአካባቢውን የውኃ አስተዳደር ተቋማትን በማጠናከር፣ የአካባቢውን ሕዝብ ባለቤትነት በማሳደግ ብሎም የወልወል ወንዝን ዘላቂ አጠቃቀም በማጎልበት የተሻለ የምግብ ሉዓላዊነት ጠቀሜታ እንደሚያገለግልም ተገልጿል።