የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ ስብሰባዎች ጎን ለጎን ከስዊድን ማዕከላዊ ባንክ ምክትል ገዢ አና ሴይም ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች ተቋማዊ ቴክኒካዊ ትብብር እና ድጋፍን በማጠናከር አስፈላጊነት ላይ ባተኮረው ውይይታቸው፥ በተለይ በተቋማዊ አቅም ግንባታ እና በዕውቀት ሽግግር ላይ በጋራ መሥራት እንደሚገባ አንስተዋል።
በተመሳሳይ ዶ/ር ኢዮብ ከሩስያ ማዕከላዊ ባንክ ተወካዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ ሁለቱ ወገኖች በብሪክስ ማዕቀፍ ለጋራ ጥቅም በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ዕድሎች እና አማራጮች ላይ ምክክራቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#ebcdotstream #ethiopia #sweden #russia