Search

ዓለም አቀፉ የክትባቶች ጥምረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ

እሑድ ጥቅምት 09, 2018 38

 

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዓለም አቀፉ የክትባቶች ጥምረት (ጋቪ) ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳኒያ ኒሽታር (ዶ/ር) ጋር በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ካለው የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የጤና ስርዓት ላይ ያለውን ትብብርን ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

አቶ አህመድ ሽዴ ድርጅቱ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ እያደረገ ያለውን የረጅም ጊዜ ድጋፍ አድንቀው የቅድመ መከላከል ስርዓትና ለዚህ የሚያስፈልግ የሰው ሀይል ልማት የሀገሪቱ የጤና ስትራቴጂ ዋና የትኩረት መስክ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በሀገሪቱ በቅርቡ እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን እና የፖሊዮ ክትባትን በአስር ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ልጆች በዘመቻ መልክ ለማዳረስ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲሁም አብራርተዋል።

ሳኒያ ኒሽታር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠርና መከላከል (አፍሪካ ሲዲሲ) እያደረገች ያለውን ድጋፍና የማህበረሰብ አቀፍ ጤና ዘርፍ ላይ እያከናወነችው ያለው ስራ በአህጉር ደረጃ ተጠቃሽ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በጤና ስርዓት አፈጻጸም በዓለም ጤና ድርጅት ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ በማለቷ እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉ ሲሆን ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #Gavi