Search

የትምህርት ቤት ምገባ የተማሪዎችን የትምህርት ቅበላ አቅም እያጎለበተው መጥቷል፡- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

ዓርብ ኅዳር 05, 2018 91

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የዘንድሮውን የትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር በይፋ አስጀመረዋል።
በክልሉ በአጠቃላይ በ67 ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የሚደረገው መርሐ ግብሩ 40 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።
ርዕሰ መስተዳድሩ መርሐ ግብሩን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት፣ ምገባው የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ እና ቅበላን ከማጎልበት ባለፈ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግሥት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ እንዲገኙ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የምገባ መርሐ ግብሩ መጠነ ማቋረጥን ለመቀነስ ትልቅ አበርክቶ እንዳለውም አብራርተዋል።
መርሐ ግብሩ ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ በማስቻል በእውቀትና በክህሎት የዳበሩ አምራች ዜጎችን ለመፍጠር እንደሚያግዝም አክለው ገልጸዋል።
መርሐ ግብሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል መንግሥት በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ