የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ካስገኛቸው ትሩፋት መካከል ዘመናዊ የንግድ ቤቶች ይገኙበታል።
በኮሪደር ልማቱ 5 ሺህ 200 የንግድ ሱቆች እና ፕላዛዎች በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ተገንብተዋል።
ከነዚህ ውስጥ 4 ሺህ 972 የሚሆኑት ለተጠቃሚዎች ተላልፈው አገልግሎት እየሰጡ ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹም በቀጣይ ቀናት ወደ ሥራ እንደሚገቡ የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

የንግድ ቤቶቹ ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት ከመሆን ባሻገር የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
የከተማዋን ኢኮኖሚ በማነቃቃት፣ የኑሮ ውድነትን በመቀነስ እና ገበያን በማረጋጋት ረገድም የጎላ አስተዋፅዖ እያበረከቱ ይገኛሉ።