Search

የማሌዥያ ኩባንያዎች የጋራ ብልፅግናን የሚያመጣ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ጥሪ አቀረቡ

ረቡዕ ኅዳር 10, 2018 193

 

የማሌዥያ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች የሚጠቀሙበት ምቹ ምኅዳር መኖሩን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።

የኢትዮጵያ እናማሌዥያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሂዷል።

ፕሬዚዳንት ታየ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፥ የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት፣ በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ ትስስር በማጠናከር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማጎልበት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

ኢትዮጵያ እና ማሌዥያ ያሏቸው ብዝኅ ኅብረ ብሔራዊነትን የተላበሱ እሴቶች ለጋራ ዕድገት እናቀጣናዊ ትብብር ልዩ ዕድል መሆናቸውን ገልጸዋል።

የማሌዥያ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች በመጠቀም የጋራ ብልፅግና እና ተጠቃሚነትን የሚወስን የልማት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

#ebcdotstream #Ethiopia #Malesia #trade #investment