የማሌዥያ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች የሚጠቀሙበት ምቹ ምኅዳር መኖሩን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።
የኢትዮጵያ እና የማሌዥያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሂዷል።

ፕሬዚዳንት ታየ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፥ የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት፣ በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ ትስስር በማጠናከር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማጎልበት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
ኢትዮጵያ እና ማሌዥያ ያሏቸው ብዝኅ ኅብረ ብሔራዊነትን የተላበሱ እሴቶች ለጋራ ዕድገት እና ለቀጣናዊ ትብብር ልዩ ዕድል መሆናቸውን ገልጸዋል።

የማሌዥያ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች በመጠቀም የጋራ ብልፅግና እና ተጠቃሚነትን የሚወስን የልማት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
#ebcdotstream #Ethiopia #Malesia #trade #investment