Search

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

ዓርብ ኅዳር 19, 2018 122

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ5ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚህ መሰረት፦
1ኛ. የሁሉንም ስፖርት መሰረተ ልማቶችን ለከተማው ነዋሪ ተደራሽ ለማድረግ እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራን በአነስተኛ ክፍያ ተመን እና በነፃ መጠቀም የሚቻልበት አሰራር ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል::
2ኛ. የጤና ተቋማት የሥራ አማካሪ ቦርድ ማቋቋሚያ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
3ኛ. በመንግስት እና የግል አጋርነት (PPP) የሚተዳዳሩ ሆስፒታሎች የቦርድ የውስጥ አሰራር ደንብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
4ኛ. ሃገራዊ ፋይዳ ለአላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ምደባ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።