ኦሮሚያ ባንክ ከወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችለውን የትብብር ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል።
ስምምነቱ ኦሮሚያ ባንክ ወደ ካፒታል ገበያ እንዲገባ እንዲሁም ባንኩ የሚፈልጋቸውን የማማከር አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑን የወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክታዊት ዳዊት ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተፈሪ መኮንን በበኩላቸው፥ ከወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር የተደረገው ስምምነት የተለያዩ ሥራዎችን መሥራት የሚያስችል እና በመተጋገዝ ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል።
በቅድስት ማሞ
#ebcdotstream #OromiaBank #WegagenCapital