Search

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬን ወደ ሀገር ቤት ገቢ ከማድረግ አኳያ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በተመለከተ ከላኪዎች ጋር መከረ

ሰኞ ኅዳር 22, 2018 146

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቡና፣ ሰሊጥ እና ጥራጥሬ ዘርፍ ከተሰማሩ ላኪዎች ጋር፤ የውጭ ምንዛሬን ወደ ሀገር ቤት ገቢ ከማድረግ (Repatriation) ጋር በተያያዘ በሚስተዋሉ ክፍተቶች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
በብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በተመራው መድረክ ላይ ባንኩ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት እና ከወጪ ንግድ የሚገኘው ገቢ በወቅቱ እና ግልጽነት ባለው መንገድ ወደ ሀገር መግባት እንዳለበት አፅንኦት ተሰጥቷል።
ባንኩ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ከመውሰዱ በፊት ገንቢ ውይይት ማድረግ እንደሚቀድም በመግለጽ፤ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት፣ የሕግ ተገዢነትን ለማጠናከር እና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጥቅም ለማስጠበቅ ከግሉ ዘርፍ ጋር በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።
ብሔራዊ ባንኩ በቀጣይም ተጠያቂነትን የማስፈን፣ ኃላፊነት የሚሰማው የወጪ ንግድ አሰራርን የማበረታታት እና የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ሥርዓቱን የማጎልበት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።