Search

ኢትዮጵያ ከ22 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

ማክሰኞ ኅዳር 23, 2018 125

ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኬንያን በማሸነፍ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን አረጋግጧል።

ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው የደረጃ ጨዋታ የኢትዮጵያ ወጣት ቡድን የኬንያ አቻውን 3 ለ 0 በማሸነፍ ነው ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የተመለሰው።

ዳዊት ካሳው፣ ቢኒያም አብርሃ እና ብሩክ እይላቸው የኢትዮጵያን ግቦች አስቆጥረዋል።

ወጣቱ አጥቂ ዳዊት ካሳው በአጠቃላይ ስምንት ግቦችን በማስቆጠር  ውድድሩን አጠናቋል።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሴካፋ ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ ለዋንጫ የሚጫወቱ ይሆናል።

በአንተነህ ሲሳይ

#Ethiopia #ebcdotstream #football