Search

የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለካፒታል ገበያ እድገት አስተዋጽኦ አድርጓል - አቶ አህመድ ሽዴ

ማክሰኞ ኅዳር 23, 2018 104

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለካፒታል ገበያው እድገት አስተዋጽኦ ማበርከቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ፡፡

ሁለተኛው ቀጠናዊ የካፒታል ገበያ ጉባኤ በአዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል መካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው የካፒታል ገበያው ከተጀመረ ቅርብ ግዜ ብቻ ቢሆነውም አመርቂ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ተመላክቷል።

ዛሬ የጀመረው ጉባኤም እያደገ የመጣውን የካፒታል ገበያ ወደፊት የሚያራምዱ ሀሳቦች እና ውይይቶች የሚደረጉበት እንደሚሆን ተጠቁሟል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚጨበጥ ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለካፒታል ገበያው እድገት አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም ካፒታል ገበያን ስለማቋቋም እያነሳን ነበር ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፤ ከጥቂት ግዜያት በኋላ ካፒታል ገበያን ጀምረን እድገቱ ላይ እየተነጋገርን እንገኛለን ብለዋል። 

በመድረኩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቹ ለኢንቨስትመንት አመቺ ሁኔታን የፈጠሩ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፤ የካፒታል ገበያው መጀመር ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ የሚረዳ አንቀሳቃሽ ሞተር እንደሆነም ተጠቁሟል።

ለ3 ቀናት የሚቆየው ጉባኤው በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ለውጦች ላይ ውይይቶች ይደረጉበታል ተብሏል።

በሳምሶን ገድሉ

#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #CapitalMarket