የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት አበርክቷል።
ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ተከትሎ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ለብሔራዊ ቡድኑ የእራት ግብዣ አድርጓል።
ወ/ሮ ሸዊት በዚሁ ወቅት፥ ቡድኑ የመንግሥት እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጠንካራ ሥራ ውጤት መሆኑን ተናግረው፤ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎውም ጥሩ ውጤት ይዞ እንደሚመለስ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጂራ እና በባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
#ebc #ebcdotstream #ethiopia #nationalteam #U17