አፍሪካ ከዘመኑ ጋር የሚራመድ የስታቲስቲክስ ስርዓት እንደሚያስፈልጋት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ19ኛው የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ተቋማት ዋና ዳይሬክተሮች የጋራ የውይይት መድረክን ባስጀመሩበት ወቅት፤ የተቀናጀ የስታቲስቲክስ መረጃ ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት መረጋገጥ መሰረት መሆኑን ጠቁመዋል።
ዘርፉን ለማዘመንም ጠንካራ እና ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት፣ ዘላቂ የፋይናንስ አቅምን ማረጋገጥ እና ትብብርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
ታማኝ እና ተቀባይነት ያለው የስታቲስቲክስ መረጃ የዕድገት አቅጣጫ ጠቋሚ በመሆኑ፣ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ እና አሰራርን መከተል እንደሚገባም አብራርተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙ የተለያዩ ተቋማት አመራሮች በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በዘርፉ ያከናወነችው ውጤታማ ሥራ ለሌሎች ሀገራት በተሞክሮነት ሊወሰድ የሚገባው መሆኑን አንስተዋል፡፡
በአሸናፊ እንዳለ