የአማራ ክልል መንግሥት እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የዘላቂ ሰላም ስምምነት አድርገዋል።
በስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እንደገለጹት፤ የሰላም ስምምነቱ ለቀጣይ የሕዝብ ሰላም እፎይታ መሠረት የሚጥል ነው፡፡
ስምምነቱ የክልሉ መንግሥት ለሰላም አማራጭ የሰጠውን ቦታ የሚያሳይ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በክልሉ ሲካሄድ የነበረው ግጭት፣ በሕዝብ ላይ ካስከተለው ምስቅልቅል ባለፈ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ውድመት ማስከተሉንም አቶ አረጋ ከበደ ጠቁመዋል።
የሕዝብና የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለመጡ አካላት አድናቆትና ክብር እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልላዊ መንግሥት ይህ ግጭት እንዲያበቃ እና የክልሉ ሕዝብ የሰላም አየር እንዲተነፍስ የተለያዩ አማራጮችን ሲጠቀም መቆየቱንም አስታውቀዋል።
በሀይማኖት ከበደ